አይ ካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ለአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የተለያዪ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። እነዚህ አገልግሎቶች የአካዳሚዉን መዋቅራዊ አደረጃጀት በተሻለ እና ተልእኮን በተገቢዉ ሁኔታ ለመፈጸም በሚያስችል መልኩ ለማዘጋጀትና ከስራ አመራር ኢንስቲትዩት ወደ አዲሱ አካዳሚ ሊያሸጋግር የሚያስችል ስትራቴጅክ ሰነድ ማዘጋጀትን ያካትታሉ። ከዚህም በተጨማሪ የተለያዪ የሰው ኅብት አስተዳደር ሰነዶችን የማዘጋጀት እና የማማከር አገልግሎት ይጨምራል፡
የሚከተሉትን የስራው ተግባራት ያካትታል፦
- የአካዳሚዉን አዲስ ዝርዝር መዋቅራዊ አደረጃጀት ማዘጋጀት
- የመዋቅራዊ አደረጃጀቱን የሚገልጽ የስራ ክፍሎችን በዝርዝር ማቅረብረብ
- የአካዳሚዉን የመሸጋገሪያ ስትራቴጂ እና የሰራተኞችን የድልድል መመሪያ ማዘጋጀት
- የሰራተኞች ጥቅማጥቅም መመሪያና የደመወዝ ፓኬጅ ማዘጋጀት
- የትምህርት፣ ስልጠና፣ ጥናትና ምርምር እና ማማከር አገልግሎቶችን የክፍያ የሚወስን የዉስጥ መመሪያዎች ማዘጋጀት
- የሰራተኛዉን ድልድል በአግባቡ የሚካሄድበትን መንገድ፣ የቅሬታ አፈታት እና እንደ አስፈላጊነቱ ሽግግሩን በተመለከተ የሚመለከቱ ጉዳዮችን ማማከር፡፡
አይ ካፒታል ከአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ጋር ለፈጠረው የስራ ቁርኝት ደስታ ይሰማዋል!
i-Capital workስ on transforming organization through different initiatives such as Corporate Strategy Development for more on this click here